• Open Daily: 10am - 10pm
    Alley-side Pickup: 10am - 7pm

    3038 Hennepin Ave Minneapolis, MN
    612-822-4611

Open Daily: 10am - 10pm | Alley-side Pickup: 10am - 7pm
3038 Hennepin Ave Minneapolis, MN
612-822-4611
Jehovah Nessi

Jehovah Nessi

Paperback

Christian Living

ISBN10: 108793740X
ISBN13: 9781087937403
Publisher: Indy Pub
Published: Feb 10 2016
Pages: 122
Weight: 0.33
Height: 0.26 Width: 5.50 Depth: 8.50
Language: Amharic

ያህዌ ንሲ - በዓላማ መኖርሰዎች ለባንዲራዬ እሞታለሁ ሲሉ፣ ለጨርቁ ማለታቸው አይደለም፤ በዚያ ሰንደቅ ለተወከለው ታሪክ፣ እሴት፣ ባህል፣ ግዛት (territory)ና ዓላማ ማለታቸው ነው። በዚያ ባንዲራ ውስጥ ብዙ ነገር ያያሉ። ከራሳቸው የሚሰፋና የሚተልቅ ነገር ያያሉ። ሙሴ እንደ ሰንደቅ ዓላማ በትሩን ከፍ ካደረገ በኋላና አማሌቅን ካሸነፈ በኋላ እግዚአብሔር ዓላማዬ ነው (ያህዌ ንሲ) የሚል መሠዊያ ሠራ። ለእግዚአብሔር ሕዝብ የድል መሠረት የሆነውን ነገር በዚህ መሠዊያ አሠመረበት። ከግብጽ የወጡ እስራኤላውያን ከራሳቸው የሚሰፋና የሚበልጥ ነገር ማየት ካልቻሉ፣ እግዚአብሔር ወዳሰበው ነገር ለመድረስና የሚፈልገውን ለመሆን ይቸገራሉ። ሰንደቅን የሚያይ ከራሱ የሰፋንና የተለቀን ነገር ማየት ይችላል። ያም ራሱን ሳይሆን ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ የሚያስችል አቋም ስለሚሰጠው በብዙ ነገር ከመጠላለፍ ይድናል (2ጢሞ 2፥4)።እስራኤላውያን ከግብጽ እንደ ወጡ ባጋጠማቸው በዚህ በመጀመሪያው ጦርነት እግዚአብሔር ዓላማዬ ነው የሚለው እንዲውለበለብላቸው ነው ያደረገው። እንዲሁ እኛም ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን እንደወጣን በውስጣችን ከፍ ብሎ ሊውለበለብ የሚገባው እግዚአብሔር ዓላማዬ ነው የሚለው ሰንደቅ ነው (ቆላ 1፥13-14)። በሕይወታችን ያሉ ሌሎች ሰንደቆች ሊወርዱና በዚህ ሰንደቅ ሊተኩ ይገባል። ይህ ሰንደቅ ከፍ ብሎ ካልተውለበለበና ካልታየን ከድቅድቅ ጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን ብንወጣም፣ ነገር ግን በጉዞአችን ውስጥ ባሉ የተለያዩ ነገሮች ተሰነካክለን ወደታሰበልን ግብ ከመድረስ እንገታለን።

Also in

Christian Living