• Open Daily: 10am - 10pm
    Alley-side Pickup: 10am - 7pm

    3038 Hennepin Ave Minneapolis, MN
    612-822-4611

Open Daily: 10am - 10pm | Alley-side Pickup: 10am - 7pm
3038 Hennepin Ave Minneapolis, MN
612-822-4611
Ayamnemna Kedmom Yalkade አያምንምና ቀድሞም ያልካደ: ስብስ&#

Ayamnemna Kedmom Yalkade አያምንምና ቀድሞም ያልካደ: ስብስ&#

Paperback

Poetry Anthologies

Currently unavailable to order

ISBN13: 9798170792719
Publisher: Independently Published
Pages: 112
Weight: 0.28
Height: 0.28 Width: 5.50 Depth: 8.50
Language: Afrikaans
ሕይወት ተሰጥቶንም እንደኾን፥ ጥንቱንም በእሳት እና ውኀ የተለወሰ ግርምቢጥነት በሆዱ ስላለ፥ በኹለት የሚጠፋፋ ነገር ተፈጥረን ቆመናልና አለመጠየም፥ አለመደባለቅ አይቻልም። ኹሌ ደስታ የለ።ሌላው ይቅርና ሞትን እንዴት ልናደርገው? ኹሌ ምሥጋና? ኹሌ መወድስ? እንዴት ኾኖ? ደሞ ለምሥጋናና መወድስ ለመወድሱ መላዕክት አንሰው ነው ወይ ሰው የሚፈጠረው? እስከመቼ እኛ ብቻ ለምናውቃት እርክስናችን፥ የዘጋንባትን የልባችንን በር፥ ከውጭ ለሚመጣ እርክስና ከበር መመለስን እንፈርዳለን? እስኩ ለእርክስናችንም በር እንስጠው ጎበዝ።

ለሕይወት ተሰጥተንም እንደኾን፥ ከሕይወት መዳፍ ምርጫ እንጂ ሌላ ምን ኖሮ ያውቃል? ከእንባ እና ሳቅ ሌላ ምን አላት ሕይወት? ከክፉ እና ደግ ሌላ የላትም። ኹሌ ኀዘን የለም። ሰርክ መራመድ ይደክማል። ማረፍ ካልታከለበት በየት በኩል? ታግለን ካሸነፍነው ይልቅ፥ ቆልፎ የጣለን አይበልጥም ወይ? እጅ መስጠትም እኮ ጀግንነት የሚኾንበት ጊዜ አለ። ከእኔ እኔ ማለት ውስጥ ራስ ወዳድነት እና ትዕቢት እንደሚፈልቅ አታውቅም? ስንቱን ክደን እንችለዋለን? ስንቱ ላይ ተሳልቀን እንረካለን?

ግጥምም እንደ ሕይወት፥ ስንስቅ ሕይወት እንደተሰጠን፥ ስናነባ ለሕይወት እንደተሰጠን፥ ከሳቀ ስቀን፣ ካነባ አንብተን የምናሻግራት የትንሣዔ ቃል ትመስለኛልች።

Also in

Poetry Anthologies